የፍቅር ቋንቋ ዓይነቶች
♥️ አካላዊ ንክኪ
የመጀመሪያ ደረጃ የፍቅር ቋንቋቸው አካላዊ ንክኪ የሆነባቸው ሰዎች አካላዊ ንክኪ የበለጠ ፍቅርን እና አድናቆት እንዲሰማችው ያደርጋል
ይህ የግድ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን እጅን መያያዝን፣ ማቀፍ፣ ክንድ/ፊትን መነካካትን እና በመንገድ ላይ ሲሆዱ ክንዶን ትከሻቸው ላይ ማድረግን ሊያካትት ይችላል።በቀላል አነጋገር አካላዊ ንክኪን የሚመርጡ ሰዎች ከአጋራቸው ጋር ለመግባባት አካላዊ ንክኪ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ እና ከአጋራቸው ጋር በአካል መቀራረባቸው አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
♥️ ስጦታዎችን መቀበል
የመጨረሻው የፍቅር ቋንቋ ስጦታዎችን መቀበል ነው፡፡ ይህ ቀዳሚ የፍቅር ቋንቋ ላላቸው ሰዎች የግድ ትልቅ ወይም ውድ ስጦታ አይጠብቁም ነገር ግን የስጦታዎን ሀሳብ ያደንቃሉ
ይህ የፍቅር ቋንቋ ያላቸው ሰዎች ስጦታውን መውደድ ብቻ ሳይሆን ሰጪው ስጦታውን ለማዘጋጀት የሚያደርገውን ጥረት ያደንቃሉ። ስጦታዎችን መቀበልን የሚያስደስተው ሰው የተቀበሉትን እያንዳንዱን ስጦታ ሊያስታውሱ ይችላሉ
♥️ የማረጋገጫ ቃላት
የፍቅር ቋንቋው የማረጋገጫ ቃላት የሆነ ፍቅርን በንግግር፣በምስጋና ወይም በአድናቆት መግለፅን ይመርጣል።በአጋሮት የተፃፉ ደግ ቃላቶች ፣አነቃቂ ጥቅሶች፣ የፍቅር ማስታወሻዎች፣ ወይም የምስጋና የጽሁፍ መልዕክቶች ያስደስቶታል። ይህን የፍቅር ቋንቋ የሚመርጡ ሰዎች ደግነት ለጎደላቸው ቃላቶች አሉታዊ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል እና ከአጋራችው ለሚሰነዘሩ ትችቶች ከመጠን በላይ ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ
የፍቅር ቋንቋው የማረጋገጫ ቃላት የሆነ አጋር ካሎት ምስጋናዎችን ማቅርብ ፣ አጋሮት በሚናገረው ነገር ላይ ፍላጎት ማሳየት እና ላከናወነው ነገር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ደስተኝ ማድረግ ይችላሉ።በጥልቅ ደረጃ ከአጋራችው ጋር ለመግባባት ‘እወድሻለሁ/ው’፣ ‘በአንተ/ቺ እኮራለሁ’ እና ‘አደንቅሃለሁ/አደንቅሽለው’ ሊሉ ይችላሉ
♥️ ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ
የፍቅር ቋንቋዎ ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ ከሆነ፣ፍቅርን የሚግልፁት ያልተከፋፈለ ትኩረቶን ለአጋሮ በመስጠት ነው፡፡ ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ የዓይን ንግግርን፣በንቃት ማዳመጥ፣በትኩረት መቆየት እና በአጋሮት ላይ ማተኮርን ያካትታል፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ሀሳቦችን፣ ልምዶችን፣ ስሜቶችን ጥልቅ ግላዊ ፍላጎቶችን፣ የማንነት ተቀባይነትን እና ያልተቋረጠ አውድን መጋራት ያሉ ጥራት ያላቸውን ውይይቶችን ሊያካትት ይችላል
ይህ የፍቅር ቋንቋ ያለው ሰው ጋር አብረዎ በሚሆኑበት ጊዜ ስልኮት ላይ የሚያተኩሩ ከሆነ፣ ሲናገር የሚያቋርጡት ከሆነ ወይም ስሜቶትን የማያከፍሉት ከሆነ እንደማይወዱት ሊሰማው ይችላል።ይልቁንም አሳቢ መሆን ፣ድጋፍ መስጥት፣ማዳመጥ እና መሳተፍ እንደሚወዱት እንዲሰማው ያደርጋል
♥️ የአገልግሎት ተግባራት
የአንድ ሰው ዋና የፍቅር ቋንቋው የአገልግሎት ተግባራት ከሆነ፣ ፍቅራቸውን ለመግለፅ ወይም አጋራቸው ፍቅሩን ለመግለፅ ከፈለገ የእርዳታ አገልግሎት መቅርብ አለበት
ይህ አጋራቸው ያልተጠበቁ ጥሩ ነገሮችን ሲያደርግ፣ ልዩ ፕሮጀክቶችን በጋራ መስራትን፣ የቤት ውስጥ ስራዎችን ማጠናቀቅ እና በአገልግሎት መረዳዳትን ይጨምራል
እነዚህ ብዙውን ጊዜ ጫናን ወይም ጭንቀትን ለማስታገስ ከመደበኛው የኃላፊነት ድርሻዎ በላይ በመሥራት አጋሮን መርዳት ሊሆን ይችላል። ይህ የፍቅር ቋንቋ ያላቸው ሰዎች አጋራቸው ነገሮችን ለማቅለል ሲል አንድ መስራት የማይወዱትን ስራ በመስራት ማስደስት ይቻላል/ፍቅርን ለመግለፅ ጥሩ መንገድም ነው





